Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

op

Office of Planning
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

የኤጀንሲ ስም፦ የዕቅድ ቢሮ
የተልዕኮ መግለጫ ፦ የዕቅድ ቢሮ ተልዕኮ የኮሎምቢያ አውራጃን እድገት ለመምራት ነው፣ በቅርብ ያሉ እና ውስን የሆኑ ጎረቤቶቻችንን መጠበቅ እና እድሳት ማከናወን፣ ውሳኔዎችን ማሳወቅ፣ የስትራቴጂክ ግቦችን ማበልፀግ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የእድገት ውጤቶች ማበረታታት፣ እና ሁሉንም የማህበረሰብ አባላት ማካተት ከተልዕኮአችን ውስጥ የሚጠቀሱት ናቸው።
ዋና ዋና ፕሮግራሞች/የክፍፍል ዝርዝር ፦ ከፍሎቻችን የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣሉ፦
የእድገት ግምገማ፦ ይህ ክፍል በአጠቃላይ ትልቅ፣ ውስብስብ፣ እና የአካባቢውን ፀባይ ለመለወጥ ምሳሌያዊ በሆኑ አቀማመጦች ላይ ዕቅዶችን ይገመግማል። ለአውራጃው እድገት እንደ የኢኮኖሚ ሞተር ስለሚታይ፣ የአጎራባቾቹን ውህደት መጠበቅም አስፈላጊ ነው። የእድገት ግምገማ ክፍል የአጎራባቾችን ስሜት እና ፍላጎት እንዲሁም እሴቶች ባማከለ መልኩ የሚደረግ እድገትን ያበረታታል።
ታሪካዊ ጥበቃ፦ ይህ ክፍል የኮሎምቢያ አውራጃን ቅርሶች ይጠብቃል፣ አካባቢያዊ ኢኮኖሚን ይደግፋል፣ እንዲሁም በከተማዋ ማስዋብ እና ታሪክ ላይ የዜግነት ኩራት እንዲኖር እንክብካቤን ያደርጋል። የታሪክ ጥበቃ ፕሮግራሞች ከታሪክ ጥበቃ ግምገማ ቦርድ ጋር በዚህ ክፍል የሚከናወን ይሆናል። የአጎራባች ዕቅድ፦ ይህ ክፍል አምስት ዋና ዋና የሃላፊነት የስራ ክፍፍሎች አሉት፦ (1) የትንሽ ቦታ ዕቅዶችን እና የዕቅድ ጥናቶችን ማዘጋጀት ፤ (2) የዕቅድን በስራ ላይ መዋል ማስተባበር እና መከታተል፤ (3) በአጎራባቾች ላይ ተፅእኖ በሚኖረው ከተማ አቀፍ የዕቅድ ተነሳሽነቶች ላይ ተሳትፎ ማድረግ፤ (4) የእድገት ፕሮጀክቶችን መቆጣጠር እና መገምገም፤ እና (5) በመሬት አጠቃቀም፣ እድገት፣ እና ዕቅድ ጉዳዮች ላይ ለተመረጡ ባለስልጣኖች እና የማህበረሰብ ባለ ድርሻ አካላት እንደ ጉዳይ አስፈፃሚ ማገልገል። እድሳት እና ዲዛይን ፦ ይህ ክፍል በአውራጃው ውስጥ ቀጣይነት ላለው የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት እና ለተሻሻለ የመኖሪ ስፍራነት ጥራት ያለውን እና ዘላቂ የሆነ ዲዛይን ስትራቴጂን ያበለፅጋል። ለኮሎምቢያ አውራጃ፣ በማዕከላዊ ዋሽንግተን እና ለህዝብ ስፍራዎች፣ ዘላቂነት፣ እና የአካባቢዎችን ዕቅድ የማውጣት ሃላፊነት አለብን። በኢኮኖሚ ንቁ የሆነ የንግድ ስፍራዎችን፣ ጠንካራ የጉርብትና ግንኙነት፣ እና በአግባቡ የተገናኘ የህዝብ ቦታን እውን ለማድረግ ነዋሪዎችን፣ የእህት ኤጀንሲዎችን፣ እና የእድገት ማህበረሰብን ተሳታፊ እንናደርጋለን። ከተማ አቀፍ ዕቅድ፦ ይህ ክፍል ለኮሎምቢያ አውራጃ የረዥም ጊዜ (የ20-ዓመት) ዕቅድን እና የፓሊሲ ውሳኔዎችን የመምራት ሃላፊነት አለበት። የከተማ አቀፍ ዕቅድ ስራን በትብብር የሚያከናውኑት ሶስቱ ክፍሎች አዳዲስ ልምዶችን ለመለየት፣ ለመተንተን፣ ለመተርጎም አና ለማብራራት በጥምረት ይሰራሉ። እንዲሁም አሁን ያሉትን እና ሃሳብ የቀረበባቸውን ፓሊሲዎች በዝርዝር ዳታ ትንታኔ ላይ መሰረት በማድረግ ይገመግማሉ። የከተማ አቀፍ ዕቅድ ክፍል የሚከተሉትን ሶስት ክፍሎች ያካተተ ነው፦ ሁሉን አቀፍ ዕቅድ፣ የአውራጃውን ሁሉን አቀፍ አካላት ዕቅድ የሚያዘጋጅ እና የሚቆጣጠር፣ አውራጃው ብቻ በህግ ማንዴት ያለው ነው።  የስነ ምድራዊ መረጃ ስርዓቶች/ የመረጃ ቴክኖሎጂ (GIS/IT)፣ የካርታ፣ የቦታ መረጃ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የGIS አገልግሎቶችን ለዕቅድ ቢሮ፣ ለሌሎች ለአውራጃ ኤጀንሲዎች፣ እና ለኮሎምቢያ አውራጃ ተጠሪዎች የሚሰጥ ነው።  የሃገር ዳታ ማዕከል፣ ለኮሎምቢያ አውራጃ የዕቅድ ቢሮ ፣ለሌሎች የአውራጃ ኤጀንሲዎች፣ እና ለኮሎምቢያ አውራጃ ነዋሪዎች የህዝብ ቆጠራ እና ሌሎች ዳታ ያቀርባል። አገልግሎቶች፦ OP ለአጎራባቾች፣ ኮሪደሮች፣ አውራጃዎች፣ ለታሪክ ጥበቃ አካላት፣ ለህዝብ አቅርቦቶች፣ ለመናፈሻዎች እና ክፍት የመዝናኛ ስፍራዎች፣ እና ለገለሰብ ሳይቶች ዕቅዶችን ያከናውናል። በተጨማሪም፣ OP በከተማ ዲዛይን፣ የመሬት አጠቃቀም፣ እና የታሪክ ጥበቃ ግምገማ ውስጥ ይሳተፋል። እንዲሁም የታሪካዊ ምንጮች ምርምርን እና የማህበረሰብ ራዕይን እናከናውናለን፣ እንደሁም የዩኤስ የህዝብ ቆጠራ ዳታን እናስተዳድራለን፣ እንተነትናለን፣ እናዘጋጃለን እንዲሁም እናሰራጫለን።
የትርጉም አገልግሎቶች፡ እባክዎ በራስዎ ቋንቋ ተጨማሪ እገዛን ለማግኘት ቢሮአችንን በስልክ ቁጥር (202) 442-7600 በመደወል ያነጋግሩ። ወደ ቢሮአችን በሚደውሉ ጊዜ ወይም ቢሮችንን በሚጎበኙ ጊዜ የእኛ መስሪያ ቤት አባል ከአስትርጓሚ ጋር እንደሚያገናኝዎት እና እገዛ እንደምናረግልዎት አርግጠኞች ነን።
የምንገኝበት አድራሻ፦
Office of Planning
1100 4th St SW
Suite E650
Washington, DC 20024
(202) 442-7600
planning.dc.gov